ይከተሉን :
Contact Us
Customer Service
Service Request
Form
FAQs
Services
Calibration & Measurements
In house Service
On Site Services
Mobile Service
Scientific Equipments Maintenance
Medical Equipment
Nuclear Equipment
Electro Mechanical Equipment
Measurement & Analysis Equipment
Training & Consultancy Service
Medical Equipment training and consultancy
Nuclear Equipment training and consultancy
Electro Mechanical Equipment training and consultancy
Measurement & Analysis Equipment training and consultancy
Accreditation
Flexible Scope
Certification of competency
Metrology Laboratories
Mechanical Metrology Laboratories
Mass Laboratory
Volume Laboratory
Density Laboratory
Pressure Laboratory
Force Machines Calibration Laboratory
Torque Laboratory
Hardness calibration Laboratory
Temperature & Chemical Metrology Laboratories
Electrical Time & Frequency Metrology Laboratories
Radiation Metrology laboratory
Dimensional Metrology Laboratories
Publications
Gallery
Plan & Report
Research & Development
References
Announcement
News
Events
Vacancy
Tender
About Us
News
Home
News
ሀገርን ብሎም ዓለምን ከጥፋት ለመታደግ ሙስናን አጥብቆ መከላከል ይገባል ተባለ፡፡
አዲስ አበባ፣ ህዳር 17/2016 ዓ.ም (ኢስኢ) የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች "ሙስና ጠላታችን ነው፤በህብረት እንታገል" በሚል መሪ ቃል ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ምክንያት በማድረግ የፓናል ውይይት አካሂደዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግርና የመወያያ ፅሁፍ ያቀረቡት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቅረአብ ማርቆስ እንደተናገሩት ሙስና የሀገርም ሆነ የግለሰብ ጥፋት ነው፡፡ ኢኮኖሚን፣ ፖለቲካን፣ ማህበራዊ ጉዳይን የሚያጠቃ የድንበር ዘለልነት ጠባይ ያለው ዓለም አቀፍ ወንጀል ስለሆነ በጋራ መከላከል ግዴታ ነው ብለዋል፡፡ እንደምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገለፃ ዓለም አቀፍ ጥፋትን ለመከላከል ሲባል ከሃያ ዓመታት በፊት በሜክሲኮ የተቋቋመ ሲሆን በኢትዮጵያም አንደአውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2007 ዓ.ም እንደተጀመረ ጠቁመው የቀኑ መከበር ዋና ዓላማ በሙስና ላይ ንቅናቄ በመፍጠር ሀገርን ወደተሻለ ደረጃ ማሻገር ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡ በሀገራችን ሙስናን ለመከላከል የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩና እርምጃዎች እየተወሰዱ ቢሆንም የሚፈለገውን ያህል ውጤት ማምጣት እንዳልተቻለ ያብራሩት አቶ ፍቅረአብ ይህን የሥነ-ምግባር ውድቀት ዋነኛ መንስኤ የሆነውን የሌብነት ተግባር መጠየፍና መግታት ከሁሉም አካል ይጠበቃል በማለት በአፅንኦት አስገንዝበዋል፡፡ በሌላ በኩል በኢንስቲትዩቱ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ፀረ-ሙስና መኮንን የሆኑት አቶ ወሠኔ መንገሻ የተቋሙን ረቂቅ የሥነ-ምግባር ኮድ አስመልክተው ሰፋ ያለ የመወያያ ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡ በመጨረሻም በኢንስቲትዩቱ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አሰፋ ተስፋዬ ሀብት ያላስመዘገቡ የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች እስከ ህዳር 30/2016 ዓ.ም ድረስ አጠናቅቀው ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ አሳስበዋል፡፡
Communication D
3 months ago
ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ተከበረ፡
አዲስ አበባ፣ መስከረም 05/2016 ዓ.ም (ኢስኢ) በተሻሻለው የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 863/2006 አንቀጽ 2 (ሁለት) መሠረት የሰንደቅ ዓላማ ቀን በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ በመጀመሪያው ሳምንት ሰኞ እንደሚከበር ተደንግጓል፡፡ የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞችም 16ኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዛሬው ዕለት ያከበሩ ሲሆን በፕሮግሮሙ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ የሰው ሀብት ልማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ አበባው እንደገለፁት ሰንደቅ ዓላማን ስናከብር ለሀገራችን ሉዓላዊነት፣ ለነፃነትና ለሰንደቃችን ክብር የተደረገውን ተጋድሎ እውቅና በመስጠት ማክበርና የጋራ መግባባት መፍጠር ህብረብሔራዊ ወንድማማችነትንና ሀገራዊ አንድነትን ለማፅናት ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡ በዓሉ"የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለህብረብሔራዊ አንድነታችንና ሉዓላዊነታችን ዋስታና ነው!" በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡
Communication D
3 months ago
ጠንካራ ተቋም ለመገንባት አቅምን አቀናጅቶ መስራት ወሳኝ እንደሆነ ተገለፀ፡
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30/2016 ዓ.ም (ኢስኢ) የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት በአሠራር ማሻሻያ ላይ የተቋሙ ሠራተኞች የሰጡትን አስተያዬት ጥናት ሪፖርት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ እርካታ ዳሰሳ ጥናት ውጤት እንዲሁም በተቋም የአሰራር ስርዓትና ባህል ግንባታ ዙሪያ አጠቃላይ የሠራተኞች ውይይት አካሂዷል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሙሉጌታ ደርበው እንደተናገሩት ተቋም ሁሌም ከግለሰብ በላይ ስለሆነ ከተንከባከብነው የሰዎች ወይም የሀገር ቤዛ ይሆናል፡፡እናም ጠንካራ ተቋም ለመገንባት አቅምን አቀናጅቶ መስራት ወሳኝና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡ እንደዋና ዳይሬክተሩ ገለፃ የተቋም አሰራር ስርዓትና ባህል ለመገንባት ጠንካራ ቡድን መሪዎችን ማፍራት፣ አቅምን አስተባብሮ መስራት፣ ከራሳችን ጀግኖች መማር፣ የስራ አርበኛ መሆን፣ የአቻ ግፊት መደላድሎችን መፍጠር፣ የስነልቦና ውቅር ግንባታ ማድረግ እንዲሁም በህጎች፣ መመሪያዎችና የአሰራር ስርዓቶች ላይ ግንዛቤን ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን በአፅንኦት አስገንዝበዋል፡፡ በሌላ በኩል በአሰራር ማሻሻያ ዙሪያ የተቋሙ ሠራተኞች የሰጡትን አስተያዬት የዳሰሳ ጥናት ሪፖርት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቅረአብ ማርቆስ በተብራራ መልኩ አቅርበዋል፡፡ እንዲሁም የደንበኞችን እርካታ የዳሰሰ ጥናት ሪፖርት እና በተቋማዊ ለውጥ ስራና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ የለውጥና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ገመቹ አመንቴ አቅርበዋል፡፡ በቀረቡት ጽሁፎች ላይ የተቋሙ ሠራተኞች ሰፋ ያለ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ለአዲሶቹ አመራሮች ሰፋ ያሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡ ለጥያቄዎቹ ምላሽና ቀጣይ የስራ አቅጣጫ የሰጡት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሙሉጌታ ደርበው ከዚህ ቀደም የነበሩ የአሰራር ችግሮችንና ክፍተቶችን በጋራ ለማረም ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀው በአመራሩና ሠራተኛው መካከል መልካም የሆነ የስራ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ተቋም ለመገንባት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡
Communication D
3 months ago
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን 116ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ተከበረ፡
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15/2016 ዓ.ም (ኢስኢ) የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች "በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት" በሚል መሪ ቃል የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የተመሰረተበትን 116ኛ ዓመት በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች አክብረው ውለዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሙሉጌታ ደርበው እንደገለፁት ቀደምት አባቶቻችን የህይወት ዋጋ ከፍለው ሀገራችንን በመጠበቅ ለእኛ አስረክበዋል፡፡ የዚህን ታላቅ የቅብብሎሽ አደራ ጠብቀን ለመጪው ትውልድ ማስረከብ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡ ዶክተር ሙሉጌታ አክለውም ሠራዊቱ የህይወት መስዋዕትነት የሚከፍል ከሆነ እኛ ደግሞ ቀላል የሆነውን የእውቀትና የጊዜ መስዋዕትነት በመክፈል ሀገራችንን በልማት ማጎልበት ይኖርብናል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡ በሌላ በኩል ከመከላከያ ሠላም ማስከበር ማዕከል የተላከን ሠነድ መነሻ በማድረግ የፓናል ውይይት የተደረገ ሲሆን ሰፊ ሀሳቦችም ተንሸራሽረውበታል፡፡
Communication D
3 months ago
‹
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
›