በኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት የተቋሙን የአይሲቲ ፖሊሲ አተገባበርና አጠቃቀም አስመልክቶ ለተወሰኑ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ
ዳይሬክቶሬት የተቋሙን የአይሲቲ ፖሊሲ አተገባበርና አጠቃቀም አስመልክቶ ለተወሰኑ አመራሮችና
ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የአይሲቲ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ኮከቤ ለማ እና የኔትዎርክ
አስተዳደር ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳንኤል ዘነበ እንደተናገሩት ፖሊሲው በ2012 ዓ.ም በተቋሙ የማኔጅመንት አባላት ፀድቆ ወደስራ
የገባ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች በተፈለገው ልክ መተግበር አልተቻለም፡፡ ፖሊሲው በአጠቃላይ በተቋሙ ውስጥ የአይሲቲ አጠቃቀምን
በተሟላ መንገድ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል፣ በምንጠቀምም ጊዜ ማድረግ ስላለብንና ስለሌለብን ተግባራት የሚገልፁ ህጎችን በዝርዝር
የሚያስረዳ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
እንደ አሰልጣኞቹ ገለፃ ይህን ፖሊሲ ተከትለን ከሰራን በራስ መተማመናችን ይጨምራል፣
የተቋሙን አጠቃላይ ደህንነት በማስጠበቅ ውጤታማ ስራ መስራት ያስችላል፡፡ ስለሆነም ሁሉም የኢንስቲትዩቱ አመራርና ሠራተኛ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂን ህግና መመሪያ ባከበረ መልኩ
መልኩ በመተግበር የተቋሙን አሰራር ዘመናዊ ለማድረግ መረባረብ ይኖርበታል፤ ለተግባራዊነቱም
ዳይሬክቶሬቱ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡
ተሳታፊዎቹ በበኩላቸው የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፖሊሲ ከተለምዷዊ አሰራር እንድንወጣ ከማስቻሉም በላይ በጥንቃቄ
አለመጠቀም በራስም ሆነ በተቋሙ ላይ ስለሚያስከትለው ጉዳት በቂ ትምህርት አግኝተንበታል ብለዋል፡፡ አክለውም ስልጠናው ለሁሉም የኢንስቲትዩቱ
ሰራተኛ መሰጠት እንደሚኖርበትና ፖሊሲውም በፍጥነት ወደ ሙሉ ትግበራ መግባት እንዳለበት ጠይቃዋል፡፡
Comments(0)