Follow Us:
Contact Us
Customer Service
Service Request
Form
FAQs
Services
Calibration & Measurements
In house Service
On Site Services
Mobile Service
Scientific Equipments Maintenance
Medical Equipment
Nuclear Equipment
Electro Mechanical Equipment
Measurement & Analysis Equipment
Training & Consultancy Service
Medical Equipment training and consultancy
Nuclear Equipment training and consultancy
Electro Mechanical Equipment training and consultancy
Measurement & Analysis Equipment training and consultancy
Accreditation
Flexible Scope
Certification of competency
Metrology Laboratories
Mechanical Metrology Laboratories
Mass Laboratory
Volume Laboratory
Density Laboratory
Pressure Laboratory
Force Machines Calibration Laboratory
Torque Laboratory
Hardness calibration Laboratory
Temperature & Chemical Metrology Laboratories
Electrical Time & Frequency Metrology Laboratories
Radiation Metrology laboratory
Dimensional Metrology Laboratories
Publications
Gallery
Plan & Report
Research & Development
References
Announcement
News
Events
Vacancy
Tender
About Us
News
Home
News
የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትምህርታዊ ጉብኝት አካሄዱ::
በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሣይንስ ትምህርት ቤት 3ኛ ዓመት የፊዚክስ ተማሪዎች ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስነ-ልክ ኢንስቲትዩት መገናኛ ግቢ በመገኘት ትምህርታዊ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ትምህርታዊ ጉብኝቱ በተቋሙ የካሊብሬሽን መሳሪያዎች አጠቃቀምና አገልግሎት ላይ የተኮረ ሲሆን በዋናነት ተማሪዎቹ የማስ ካሊብሬሽን፣ የኤሌክትሪካል፣ የግፊት፣ የይዘት እና የሙቀት ካሊብሬሽን ላብራቶሪ ክፍሎችን ተመልክተዋል፡፡ ጉብኝቱን ካደረጉ ተማሪዎች መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያዬት ይህ ትምህርታዊ ጉብኝት እስካሁን በንደፈ-ሀሳብ የተማርነውን ትምህርት በተግባር በማጠናከር የበለጠ እውቀት እንድናካብት ብሎም ተመርቀን ስንወጣ ለሀገራችን ውጤታማ ስራ እንድንሰራ በማድረግ ረገድ የጎላ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል፡፡ በኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ የሜካኒካል ካሊብሬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ ሰለሞን አሰፋ እንዲሁም የላብራቶሪ ክፍል ባለሙያዎች ላደረጉት በእውቀት ላይ የተመሰረተ ገለፃ እንዲሁም ጉብኝቱን ለፈቀዱ የተቋሙ አመራሮች ምሥጋና ይገባል ሲሉ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ በጉብኝቱ ላይ አስር ተማሪዎች እና ሦስት አስተባባሪ መምህራን ተሳትፈዋል፡፡
communication.D
1 month ago
በህጋዊ ስነ-ልክ ዙሪያ ለንግድ ቢሮ ኃላፊዎችና ለህጋዊ ስነ-ልክ ባለሙያዎች በሀዋሳ ከተማ ሲሰጥ የነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተጠናቀቀ፡፡
የኢትዮጵያ ስነ-ልክ ኢንስቲትዩት በጥራት መሰረተ ልማት፣ በልኬት መሰረታዊ ሀሳብ፣ በስነ-ልክና በህጋዊ ስነ-ልክ ምንነት ዙሪያ ለሲዳማና ለደቡብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት የንግድ ቢሮ ኃላፊዎችና ለህጋዊ ስነ-ልክ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ በፕሮጋረሙ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ስነ-ልክ ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ አብዱራህማን ፣የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ንግድና ኢንዱስትሪ ም/ቢሮ ኃላፊና የንግድ አሰራር ሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ባጥሶ ዌድሶ እንዲሁም የደቡብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የንግድ ኢንስፔክሽንና ሬጉሌሽን ዳይሬክተርና ተወካይ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቸርነት ፈቃዱ በተከታታይ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡ በዚሁ መሰረት የኢትዮጵያ ስነ-ልክ ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ አብዱራህማን እንደገለፁት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በልኬት ሳይንስ ዘርፍ ተወዳዳሪ እንድትሆን በተለይ አምራቹና አገልግሎት ሰጪ ኢንዱስትሪው የሚያመርቷቸው ምርቶች ጥራት እንዲኖራቸው ብሎም ወጥነትና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው የአለካክ ሥርዓት በመዘርጋት ፍትሀዊ የንግድ ስርዓት እንዲኖር እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ አክለውም ይህን ስራ ማሳካት የሚቻለው እንደዚህ አይነት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በማዘጋጀት ቴክኒካዊ ብቃትና በስነ-ምግባር የታነፀ ባለሙያ ማፍራት ሲቻል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም መድረኩ የተሳካ እንዲሆን ሁለቱ ክልሎች ላደረጉት ትብብር ምስጋና ያቀረቡት ዳይሬክተሩ በቀጣይም ኢንስቲትዩቱ በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ በሌላ በኩል የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ንግድና ኢንዱስትሪ ም/ቢሮ ኃላፊና የንግድ አሰራርና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ባጥሶ ዌዲሳ እና የደቡብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የንግድ ኢንስፔክሽንና ሬጉሌሽን ዳይሬክተርና ተወካይ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቸርነት ፈቃዱ እንደተናገሩት የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ በናረበትና ብዙ የልኬት ማጭበርበር ወንጀሎች በሚፈፀሙበት በዚህ ወቅት ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መዘጋጀቱ ጠቀሜታው ከፍ ያለ መሆኑን አውስተዋል፡፡ አንዳንድ የንግድ ተቋማት የልኬት መሳሪያዎችን በመቀሸብና ክብደትን በማሳነስ ህብረተሰቡን እያማረሩ እንደሚገኙና መንግስት የሚመራውን ህዝብ ደህንነት የማስጠበቅ ግዴታ ስላለበት በእነዚህ ህገወጦች ላይ እርምጃ መወሰዱንና በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኃላፊዎቹ ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም የኢትዮጵያ ስነ-ልክ ኢንስቲትዩት ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ አብዱራህማን የተቋሙን አመሰራረትና አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ አስመልክተው ገለፃ ያደረጉ ሲሆን በሌላ በኩል በኢንስቲትዩቱ የዋና ዳይሬክተር አማካሪና የኤሌክትሪካል ጊዜና ድግግሞሽ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ነስረዲን ነዚር እንዲሁም ከፍተኛ የሜካኒካል ካሊብሬሽን ባለሙያ አቶ ሰለሞን አሰፋ የግንዛቤ ማስጨበጫውን ሰጥተዋል፡፡ ርዕሰ ጉዳዮችም ስነ-ልክና በጥራት ላይ የሚጫወተው ሚና፣ ስለህጋዊ ስነ-ልክ ምንነት፣ ፋይዳዎች፣ የስነ-ልክ ሕግ አወጣጥ መሰረታዊያን፣ የተለመዱ የቁጥጥር ተግባራት ፣ ለህጋዊ ስነ-ልክ ኦፊሰሮችና በኦፊሰሮች ቁጥጥር የሚደረግባቸው መሳሪያዎች፣ የነዳጅ መቅጃ ዲስፔንሰር ቬሪፊኬሽን፣ የሚዛኖች ቬሪፊኬሽን እና የክብደት ማነፃፀሪያዎች ቬሪፊኬሽን የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች መሆናቸውን መረዳት ተችሏል፡፡ በመጨረሻም በከተማው በሚገኝ አንድ የነዳጅ ማደያ ላይ የተግባር ልልምድ የተደረገ ሲሆን ከተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተው ከመድረክ ምለሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
communication.D
2 months ago
ዓለማቀፉ የስነ-ልክ ቀን እየተከበረ ነው፡
የኢትዮጵያ ስነ-ልክ ኢንስቲትዩት ለተቋሙ ማህበረሰብ፣ ደንበኞች እና በዚህ ዘርፍ ለተሰማሩ ሁሉ በየአመቱ በኢትዮጵያ ግንቦት 12 ወይም በፈረንጆች ግንቦት 20 ለሚከበረው ዓለም አቀፍ የስነ-ልክ ቀን እንኳን በሠላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡ የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የስነ-ልክ ቀን "ስነ-ልክ በዲጂታል ዘመን" /Metrology in the Digital Era/ በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡
communication afairs
2 months ago
በዘመናዊ የሀብት ምዝገባ መረጃ ሥርዓት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡
የኢትዮጵያ ስነ-ልክ ኢንስቲትዩት የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍል በዘመናዊ የሀብት ምዝገባ መረጃ ስርዓት፣ በፌዴራል የስነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ እና በተሻሻለው የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ አፈፃፀም መመሪያ ዙሪያ ለኢንስቲትዩቱ አመራሮችና ሠራተኞች ስልጠና ሠጥቷል፡፡
communication afairs
2 months ago
‹
1
2
›