ይከተሉን :
Contact Us
Customer Service
Service Request
Form
FAQs
Services
Calibration & Measurements
In house Service
On Site Services
Mobile Service
Scientific Equipments Maintenance
Medical Equipment
Nuclear Equipment
Electro Mechanical Equipment
Measurement & Analysis Equipment
Training & Consultancy Service
Medical Equipment training and consultancy
Nuclear Equipment training and consultancy
Electro Mechanical Equipment training and consultancy
Measurement & Analysis Equipment training and consultancy
Accreditation
Flexible Scope
Certification of competency
Metrology Laboratories
Mechanical Metrology Laboratories
Mass Laboratory
Volume Laboratory
Density Laboratory
Pressure Laboratory
Force Machines Calibration Laboratory
Torque Laboratory
Hardness calibration Laboratory
Temperature & Chemical Metrology Laboratories
Electrical Time & Frequency Metrology Laboratories
Radiation Metrology laboratory
Dimensional Metrology Laboratories
Publications
Gallery
Plan & Report
Research & Development
References
Announcement
News
Events
Vacancy
Tender
About Us
News
Home
News
የሳይንስ መሳሪያዎች ስልጠናና ምክር ዳይሬክቶሬት በአናሎግና ድጂታል ኤሌክትሮኒክስ ዙሪያ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡
አዲስ አበባ፣ ጥር 13/2016 ዓ.ም (ኢስኢ) የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት የሳይንስ መሳሪያዎች ስልጠናና ምክር ዳይሬክቶሬት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በመተባር ከከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮዎች ለተወጣጡ የባዮሜዲካል ኢንጂነሮች ያዘጋጁትና በአናሎግ እንዲሁም በድጂታል ኤሌክትሮኒክስ ላይ ያተኮረ ስልጠና ዛሬ ተጀምሯል፡፡ ስልጠናውን ብንግግር የከፈቱት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሙሉጌታ ደርበው እነኳን እንድትገለገሉበት በሚያስፈልጋችሁ ቴክኖሎጂ እየገገነባነው ወዳለው የጋራ ኢንስቲትዩታችን በደህና መጣችሁ። ስልጠናውን ስናዘጋጅ በበቂ ምክክር በመሆኑ ለስራችሁና ለቀጣይ ስልጠናዎች መሰረት ይጥላል የሚል እምነት አለኝ ብለዋል። በተለይ የሚከፈለንን ክፍያ ለምንሰራው ስራ ማነፃፃሪያ ሳናደርግ፤ አጃችን ላይ ያለውን የማገልገል እድል በተቋሞቻችን የተደረራጁ ቴክኖሎጂዎችን እና የመንግስት የስራ ሰዓትን በውጤታማነትና በቅልጥፍና መጠቀም ላይ ማተኮር አለብን፡፡ በመንግስት ቤት ስንሰራ ትልቁ ቱርፋታችን ህዝባችንና ሀገራችንን ማገልገል ሲሆን በዚሁ እየረካን፤ በምናገኛቸው የስልጠናና የትምህርት እድሎች እራሳችንን በእውቀትና በክህሎት ማብቃት እንደሆነ ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል ሲሉ አስረድተዋል። ስልጠናው በየጤና ተቋማቱ የህክምና መሳሪዎች እያሉ ባልተገባ የጥገና ውስንነት የሚስተጓጎል የህክምና ሂደት እንዳይኖር የሚፈለገውን ክህሎት ሳይቆራረጥ በጋራ ለመገንባት መሰረት ይጥላል ብለን እናስባለን። ይህ ግንኙነታችን የጤናው ዘርፍ ሴክተር መስሪያ ቤቶችና የስነ-ልክ ኢንስቲትዩት በሀገራችን የህክምና መሳሪዎችን የአጠቃቀም ውጤታማነትንና ዘመናዊነትን ለማረጋገጥ ተቀራርበን እና ተቀናጅተን የምንሰረበትን ምእራፍ እንደ አዲስ የምንከፍትበት ይሆናል። በስልጠናው የምትሹትን የምታሳኩበት፣ ሰልጣኞች ከአሰልጣኞች እና ሰልጣኞች እርስ በእርሳችሁ የሙያ ወንድማማችነት የምታፈሩበት እንዲሆን እንመኛለን ሲሉ ገልፀዋል። ለዚህ ስኬት አብረውን ለሰሩት የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ የሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ስልጠናው እንዲሳካ ጥልቅ እና ሙያዊ ጥረት ያደረገውን በኢንስቲትዩታችን የሳይንስ መሳሪያዎች ስልጠናና ምክር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢነጂነር አበባየሁ ማሞንና የዳይሬክቶሬቱን ባለሙዎች በሙሉ ከልብ ማመስገን እወዳለሁ ብለዋል። የሳይንስ መሳሪያዎች ስልጠናና ምክር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንጂነር አበባየሁ ማሞ በበኩላቸው የክፍሉን ተግባራት ያብራሩ ሲሆን በዚህ መሰረት የሳይንስ መሳሪያ ተጠቃሚዎች ተግባሮቻቸውን በብቃት እንዲያከናውኑ ለማስቻል ከአቅማቸው በላይ ለሆኑ ሳይንስ መሳሪያዎች ተከላ፤ ኮሚሺኒንግ፤ ጥገናና ማስወገድ ስራዎችን በመስራት የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት እንዲሁም በህክምና መሳሪያዎች ተከላ፤ኮሚሺኒንግና ጥገና ስራ ለተሰማሩ ወርክሾፖች የብቃት ማረጋገጫ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡ እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ይህ ስልጠና በአናሎግና ድጂታል ኤሌክትሮኒክስ ላይ ትኩረት ያደረገ እና ለተከታታይ ሳምንታት በአራት ዙር ስድሳ ለሚሆኑ በከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ ስር ለሚገኙ የባዮሜዲካል ኢንጂነሮች እንደሚሰጥ ጠቁመው ተሳታፊዎች ስልጠናውን በትኩረት በመከታተል በቂ እውቀት መጨበጥ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የመድሀኒትና ሕክምና መሣሪያዎች አቅርቦትና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰይፈ ደምሴ እንደተናገሩት ከዚህ በፊት በከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ ስር የሚገኙ የህክምና መሳሪያዎች አገልግሎት የሚሰጡት ከ50 በመቶ የማይበልጡ ነበሩ፡፡ ጤና ቢሮው ችግሩን በመረዳት ባከናወነው ጠንካራ ሥራ አሁን ላይ ከ85 በመቶ በላይ የሚሆኑ የህክምና መሳሪያዎች አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙና ይህ ባይሳካ ኖሮ ይወጣ የነበረውን ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግስት ሀብት ማዳን መቻሉንም አስረድተዋል፡፡ አቶ ሰይፈ እንዳሉት ከኢንስቲትዩቱ ጋር ከረጅም ዓመታት አንስቶ ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው ጠቅሰው ችግሮችን እንድንፈታ እና የተሟላ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን ጤና ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት ኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልፀው ሠልጣኞችም ይህን እድል በአግባቡ በመጠቀም ከመሳሪያዎች ጥገና ባሻገር ወደፊት ለሚኖረን የቴክኖሎጂ ፈጠራ መዘጋጀት ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡ በመጨረሻም ዳይሬክተሩ ባለሙያዎቻችን ይህን ስልጠና እንዲወስዱ ለአማቻቹልን የኢንስቲትዩቱ አመራሮች ምሥጋና እናቀርባለን ብለዋል፡፡
Communication D
3 months ago
የቦሌ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ትምህርታዊ ጉብኝት አካሄዱ:
የቦሌ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ጥር 7 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስነ-ልክ ኢንስቲትዩት መገናኛ ግቢ በመገኘት ትምህርታዊ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ትምህርታዊ ጉብኝቱ በተቋሙ የካሊብሬሽን መሳሪያዎች አጠቃቀምና አገልግሎት ላይ የተኮረ ሲሆን የተለያዩ ላብራቶሪ ክፍሎችን ተመልክተዋል፤ተግባራቸውን አስመልክቶም በክፍሉ ባለሙያዎች ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡ ጉብኝቱን ካደረጉ ተማሪዎች መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያዬት ይህ ትምህርታዊ ጉብኝት በንደፈ-ሀሳብ የተማርነውን ትምህርት በተግባር በማጠናከር የበለጠ እውቀት እንድናካብት እና ወደፊት ለሀገራችን ውጤታማ ስራ እንድንሰራ በማድረግ ረገድ የጎላ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም የኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች ላደረጉት በእውቀት ላይ የተመሰረተ ገለፃ እንዲሁም ጉብኝቱን ለፈቀዱ የተቋሙ አመራሮች ምሥጋና ይገባል ሲሉ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ በጉብኝቱ ላይ 120 ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
Communication D
3 months ago
አራቱ የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት ያዘጋጁት የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ተካሄደ፡
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25/04/2016ዓ.ም(ኢስኢ) አራቱ የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት ያዘጋጁትና አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች እንዲሁም የመንግሥት ተቆጣጣሪ አካላት የተሳተፉበተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ሐሙስ ታህሳስ 25 ቀን 2016ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ተካሂዷል፡፡ ግንዛቤ ማስጨበጫውን በንግግር የከፈቱት የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መዓዛ አበራ እንደተናገሩት በሀገራችን ፍጣንና ተከታታይነት ያለው የኤኮኖሚ ዕድገት ለማምጣት የምርትና አገልግሎትን ጥራት ማረጋገጥ ዋሳኝ ድርሻ አለው፡፡ ከዚህ አንፃር ምርቶችና አገልግሎቶችን በወጡላቸው ስታንዳርዶች(መመዘኛዎች) መሰረት ማምረትና አገልግሎት መስጠት በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪና አሸናፊ ለመሆን ዋነኛ መንገድ ነው፡፡ ወ/ሮ መዓዛ ጨምረው እንዳሉት ከመረጃ ልውውጥ ፍጥነት የተነሳ ዓለም አንድ መንደር ሆናለች፤ የምርቶች ጥራትና ተወዳዳሪነትም በእጅጉ አይሏል፡፡ ይህንን እውነታ ከግንዛቤ ያስገባው መንግሥት አራቱን የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት ስትራቴጂካዊ በሆነ መንገድ በማደራጀት አምራችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ጥራታቸውን የጠበቁና ተወዳዳሪ ምርትና አገልግሎቶችን እንዲያቀርቡ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ ከመክፈቻ ንግግሩ በማስቀጠል የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማቱ ተወካዮች ስለሚሰጧቸው አገልግሎቶችና ደረጃዎች፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ ቀጣይ ዕድሎችና ተስፋዎች በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን የአንድ ተጋባዥ ተቋም የሥራ ኃላፊም በምግብ ምንነትና ደህንነት ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል፡፡ የኢትጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩትን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገመቹ አመንቴ እንደገለጹት ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ከጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት አንዱ ሲሆን የካሊብሬሽን እና የሳይንስ መሳሪያዎች ቴክኒክ፣ጥገና፣ ስልጠናና ማማከር ተግባራትን ያከናውናል፡፡ አቶ ገመቹ ጨምረው እንዳሉት በካሊብሬሽን ዘርፍ ከስድስት በላይ በሆኑ ፓራሜትሮች ዓለማቀፍ ዕውቅና ያለው ስለመሆኑ ተናግረው በኢን-ሃውስ፣ በሞባይልና በመስክ በመላው ሀገሪቱ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ ጨምረውም በሳይንስ መሳሪያዎች ዘርፍም በተለይ ከሕክምና መሳሪያዎች ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የጥገና አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝና በስልጠና ዘርፍም የባዮሜዲካል ኢንጂነሮችን በየዓመቱ እንደሚያሰለጥንና ለተለያዩ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሥራ ላይ ልምምድ እንደሚሰጥም ተናግረዋል፡፡
Communication D
3 months ago
ኢንስቲትዩቱ በሁለት የጥናት ፕሮፖዛሎች ላይ ውይይት አካሄደ፡
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 02/2016 ዓ.ም (ኢስኢ) የኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት በሳይንስ መሣሪያዎች ቴክኒክና ምህድስና ዳይሬክቶሬት ምርምር በተደረገባቸው ሁለት የጥናት ፕሮፖዛሎች ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡ የጥናት ፕሮፖዛሎቹ ‘Design and Prototype of Solar Direct Vaccine Refrigerator’ እና ‘Design and Prototype of Switch Mode Power Supply’ የተሰኙ ርዕሰ ጉዳዮችን የዳሰሱ ናቸው፡፡ የመጀመሪያውን የጥናት ፕሮፖዛል ያቀረቡት የሣይንስ መሣሪያዎች ቴክኒክና ምህንድስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንጂነር ትርፌሳ ፈይሳ እንደገለፁት በሀገራችን አብዛኞቹ ገጠራማ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ሀይል ተጠቃሚ ባለመሆናቸው በመዳህኒት ማቀዝቀዣ ፍሪጅ እጦት ምክንያት ክትባቶችና መሰል መዳህኒቶች የቆይታ ጌዜአቸው የሚያጥርበት ሁኔታ አለ ፡፡ ጥናቱም ይህን ችግር ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በፀሀይ ሀይል የሚሰራ የመዳህኒት ማቀዝቀዣ ፍሪጅ በመስራት ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ በማሰብ ነው ብለዋል፡፡ እንደ ኢንጂነሩ ማብራሪያ ማሽኑ ከሚሰጠው ከፍተኛ ጥቅም ባሻገር በአነስተኛ ወጪ የሚገጣጠም እና የውጭ ምንዛሬን በማስቀረት ረገድ የጎላ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል ‘Design and Prototype of Switch Mode Power Supply’ የሚለውን ፕሮፖዛል ያቀረቡት በሣይንስ መሣሪያዎች ቴክኒክና ምህንድስና ዳይሬክቶሬት የልኬትና አናሊስስ ቡድን መሪ የሆኑት ኢንጂነር የማነ ተስፋዬ እንዳሉት በየትኛውም የስራ ቦታ ሆነ መኖሪያ ቤት ፓወር ሳፕላይ እንጠቀማለን፡፡ እንደሚታወቀው በሀገራችን የኤሌክትሪክ ሀይል መቆራረጥ ድግግሞሽ ከፍተኛ በመሆኑ ብዙ ጊዜ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችና ከፍተኛ ማሽኖች በሚደርስባቸው ጉዳት ምክንያት ከአገልግሎት ውጪ ስለሚሆኑ ጥናቱ ይህን ችግር በመቅረፍ ረገድ ጠቀሜታ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡ እንደ ቡድን መሪው ገለፃ ይህ ምርምር እቃው የሚጠቀመውን የኤሌክትሪክ መጠን /ዋት/ ፍጆታ ማመጣጠን ወይም መቆጣጠር ያስችላል፡፡ ኢንጂነሩ አክለውም ፓወር ሳፕላዩን በሀገር ውስጥ ምርት መተካትና የውጭ ምንዛሬን ማስቀረት ስለሚችል ጠቀሜታው ዘርፈብዙ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በቀረቡት የጥናት ፕሮፖዛሎች ላይ ለአጥኝ ቡድኑ ጥያቄዎችና የማሻሻያ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን በቡድኑ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ በመድረኩ ላይ ተገኝተው የስራ አቅጣጫና ማጠቃለያ የሰጡት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሙሉጌታ ደርበው እንደተናገሩት ፕሮፖዛሉ እጅግ የሚደነቅና የሚበረታታ ነው፤ምርምሩን ላደረገው የጥናት ቡድንም ምስጋና ይገባል ብለዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ወደፊት የጥናት ማዕከል እንደሚሆን ስለሚጠበቅ መነሻ የሚሆኑ ጥናቶች መቅረባቸው በቀጣይ አቅማችንን አጠናክረን የተሻለ ሥራ እንደምንሰራ አመላካች ነው ሲሉ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ እንደዋና ዳይሬክተሩ ማብራሪያ ወጣቶች ከአንጋፋ ባለሙያዎች ልምድ መቅሠምና ራሳቸውን ማብቃት ይኖርባቸዋል፡፡ እነዚህ ምርምሮች ተጠናቅቀው ለውጤት እንዲበቁ ተቋሙ ከሌሎች ተባባሪ አካላት ጋር በመሆን እገዛዎችን ያደርጋል፡፡ የጥናት ቡድኑም በትኩረት እንዲንቀሳቀስ አሳስበዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የኢንስቲትዩቱን ም/ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ ሌሎች ባለሙያዎችም ተሳትፈዋል፡፡
Communication D
3 months ago
‹
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
›