በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሣይንስ ትምህርት ቤት 3ኛ ዓመት የፊዚክስ ተማሪዎች ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስነ-ልክ ኢንስቲትዩት መገናኛ ግቢ በመገኘት ትምህርታዊ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

.በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሣይንስ ትምህርት ቤት 3ኛ ዓመት የፊዚክስ ተማሪዎች ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስነ-ልክ ኢንስቲትዩት መገናኛ ግቢ በመገኘት ትምህርታዊ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ትምህርታዊ ጉብኝቱ በተቋሙ የካሊብሬሽን መሳሪያዎች አጠቃቀምና አገልግሎት ላይ የተኮረ ሲሆን በዋናነት ተማሪዎቹ የማስ ካሊብሬሽን፣ የኤሌክትሪካል፣ የግፊት፣ የይዘት እና የሙቀት ካሊብሬሽን ላብራቶሪ ክፍሎችን ተመልክተዋል፡፡ ጉብኝቱን ካደረጉ ተማሪዎች መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያዬት ይህ ትምህርታዊ ጉብኝት እስካሁን በንደፈ-ሀሳብ የተማርነውን ትምህርት በተግባር በማጠናከር የበለጠ እውቀት እንድናካብት ብሎም ተመርቀን ስንወጣ ለሀገራችን ውጤታማ ስራ እንድንሰራ በማድረግ ረገድ የጎላ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል፡፡ በኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ የሜካኒካል ካሊብሬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ ሰለሞን አሰፋ እንዲሁም የላብራቶሪ ክፍል ባለሙያዎች ላደረጉት በእውቀት ላይ የተመሰረተ ገለፃ እንዲሁም ጉብኝቱን ለፈቀዱ የተቋሙ አመራሮች ምሥጋና ይገባል ሲሉ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ በጉብኝቱ ላይ አስር ተማሪዎች እና ሦስት አስተባባሪ መምህራን ተሳትፈዋል፡፡
Comments(0)